የህብረት ስራማህበሩ መጋቢት 15/2011 ዓ/ም ገንዘብ መቆጠብና ማበደረን መሰረት አድርጎ 100 አባለት በሚሆኑ ወጣት ምሁራን ተመሰርቷል፡፡በዚህ ተቋም የሌለ የሙያ ዘርፍ የለም፡-ዶክተሮች( የህክምና ባለሙያዎች፣የባንክ ባለሙያዎች፣የታክስ ባለሙያዎች፣ጠበቃዎች፣አስተማሪዎች፣ነጋዲዎች ብቻ እሰከ መጻህፍት አዟሪዎችና ጉልት ቸርቻሪ የሙያ ዘርፎች ድረስ የህብረት ስራማህበሩ አባል ናቸው፡፡

ተቋሙ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ሲሆን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ500 በላይ አባላትን ያፈራ ሲሆነ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለቋል፡፡በስሩ የተደራጀ የሰው ሀይል ሲኖረው በአዲስ አበባ ሁለት ቢሮዎችን ማለትም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዘነበወርቅ አካባቢዋና መ/ቤቱ ሲሆን መገናኛ ገነት ኮሞርሻል ህንጻ ላይ ተጨማሪ ቢሮ በመክፈት ለአባላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ ድርጅት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በርከት ባሉ ሀገራዊ ማህበራዊ ተግባራት ላይ ተሳትፎ አድርጓል፡፡ አባላትን በመቀስቀስ በማስተባበር የገንዘብ ቁጠባ አቅማቸው ከፍ እንዲልና የኢንቨስትመንት ፍላጎታቸው እንዲጨምር እንዲሁም ትጋትንና መነሳሳት እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

#በተጨማሪም የአባላትን ጤና ለመጠበቅና አቅማቸውን ባማከለ መንገድ ህክምና ለመስጠት እንዲቻል በስሩ ባሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የ24ሰዓት የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱገበያ አካባቢ ፍኖት መካከለኛ ክሊኒክ ከፍቶ በአዲሱ ዓመት ስራጀምሯል፡፡

በተመሳሳይ አባላትን በዘርፋቸው በማስተባበር በትምህርቱ መስክ ለመሰማራት ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቋል ፡፡

ተቋሙን የሀገሪቱ ህግ እስከ ፈቀደ ድርስ ወደ ባንክ ዘረፍ ለማሳደግ የተቋሙ አመራሮችም ሆነ አባላት ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ::

ውድ አንባቢያን እናንተም የተቋማችን አባል ሆናችሁ በመቆጠብ ህልማችሁን እውን አድርጉ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እናመሰግናለን ! በሌላ የተቋሙ መረጃ እንመለሳለን

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *